የበጀት ዝግጅት ሂደቱ ውስጥ የበጀት ማርቀቅ ስብሰባ አንዱ ክፍል ነው፡፡ ይህም ስብሰባ የፌደራሉ የህዝብ አካላት ለገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የበጀት ጥያቄዎቻቸውን የሚቀርቡበትንና የሚያስረዱበት መድረክ ይከፍትላቸውና ሚኒስቴሩ የተጠየቀውን በጀት ወደማርቀቅ ሂደቱ እንዲገባ መንገድ ይከፍታል፡፡ ይህም መረጃ ለበጀት ማደላደል መሰረት ሲሆን ሁሉም የአስተዳደራዊ እርከኖች የበጀት ሂደቱ ላይ በደንብ እንዲነጋገሩና ባለው የገንዘብ መጠን ትክክለኛ የሆነ የበጀት አደላደል መንገድ እንዲያወጡ ይረዳል፡፡