ልማትን፣ ድህነትን እና የዜጐች ደህንነትን በተመለከተ የኢትዮጵያ የድህነት ቅነሳ ስትራቴጂ እጅግ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ ነው፡፡ ባለፉት 5 ዓመታት ውስጥ በአማካይ 11.8% አመታዊ ዕድገት ተመዝግቧል፡፡ ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢም ቀድሞ ከነበረበት $140 ወደ $205 አድጓል፡፡ እንዲህ ያለው ውጤት ሊመዘገብ የቻለው አጠቃላይ ምጣኔ ሀብቱ በግብርናው ዘርፍ እንዲመራ በመደረጉ ነው፡፡ ስለዚህም የግብርናው ዘርፍ በ2007/2008 እአአ 7.5% ዕድገት አስመዝግቧል፡፡ በቀጣዩ አመት ደሞ 6% ዕድገት ይጠበቃል፡፡ ሌሎቹም የምጣኔ ሃብቱ ዘርፎች የማይተካ ሚናቸውን በሚገባ እየተጫወቱ ነው፡፡ ለምሳሌ የኢንደስትሪው ዘርፍ 10.4% የአገልግሎቱ ዘርፍ ደግሞ 17.0% የሆነ እድገት አስመዝግበዋል፡፡ በማህበራዊ ገዕታው ደግሞ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት መስፋፋት፣ የክትባት ሽፋን መጨመር እንዲሁም የህዝቡ አመጋገብ መሻሻልን የመሳሰሉ ውጤቶች ታይተዋል፡፡
እነዚህ ሃቆች ምን ይነግሩናል?
እነዚህ ሃቆች ሃገሪቱ በከፍተኛ ፍጥነት እድገት ላይ መሆኑን፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶችን ለማዳረስና በምግብ እህል ራስን ለመቻል የመሰሉ ግቦችን በተገቢ መንገድ እየተፈፀሙ እንደሆኑ፣ የአገር ውስጥ ንግድ እንዳደገና የሚሰበሰበውም ታክስ እንደጨመረ ይነግሩናል፡፡
መረጃ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ1999 ዓ.ም 11.4% የሚሆን ዓመታዊ እድገት ሲያሳይ ከ1996-1999 ዓ.ም ባለው ጊዜ ደግሞ አማካይ አመታዊ እድገት 11.7% ነበር፡፡