Embelem of Federal Democratic Republic of Ethiopia Official Portal of Ministry of Finance and Economic Development  
Home Home Citizens Citizens Government Government Business Business Donors Donors Decrease font Increase font

 ተጠሪ መስሪያ ቤቶች

 የዘርፉ ዕይታ

 

የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ የባንኪንግ ስርዓትን፣ የኢንሹራንስ እና ጥቃቅን የገንዘብ ተቋማት ባንኮችን እና ሌሎች በመንግስት እና በግል ይዞታ ስር ያሉ አገልግሎት የሚሰጡ አካላትን የያዘ ነው፡፡ የንግድ ባንክ አገልግሎቶች በመላ ሃገሪቱ 487 ቅርንጫፍ ባላቸው 2 መንግስታዊ፣ 8 የግል እና አንድ የህብረት ስራ ባንክ ይሰጣሉ፡፡ በተጨማሪም አንድ ልዩ መንግስታዊ ባንክ አለ፡፡

 

የኢንሹራንስ አገልግሎት 9 የግል እና 1 የመንግስት የኢንሹራንስ ድርጅት ያካተተ ነው፡፡ በመላ ሃገሪቱም 146 ቅርንጫፎችም አሏቸው፡፡ እንዲሁም 28 ጥቃቅን የገንዘብ ተቋማት እና ሌሎች ጥቂት የማይባሉ የቁጠባ ተቋማት እና የህብረት ስራ ማህበራት አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ ሁሉም የንግድ ባንኮች የቁጠባ፣ የተንቀሳቃሽ ሒሳብ፣ የአጭር ግዜ ብድርን ማራዘም፣ አስተማማኝ የሆነ አገልግሎት መስጠትና ከነዚህ ጋር አብረው የሚሄዱ ሌሎች የንግድ ባንክ አገልግሎቶችን ይሰጣሉ፡፡

 

ባህላዊ መንገድ የተመዘገቡ እና በሃገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ካምፖኒዎችም እንደ ኢትዮጵያውያኑ ድርጅቶች ሁሉ የሃገር ውስጥ ብድር ተጠቃሚ የመሆን መብት አላቸው፡፡