Embelem of Federal Democratic Republic of Ethiopia Official Portal of Ministry of Finance and Economic Development  
Home Home Citizens Citizens Government Government Business Business Donors Donors Decrease font Increase font

 ተጠሪ መስሪያ ቤቶች

 ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች

የልማት ኘሮጀክቶች ሥርዓትና የሥርዓቱ ማስፈፀሚያ ሜቴዶሎጂዎች

የልማት ኘሮጀክቶች የሚመሩበት ሥርዓት አላቸው፡፡ ሥርዓቱን መሠረት በማድረግ የልማት ዓላማዎችን ለማስፈፀምና በተወሰነ መልካ ምድራዊ በጥናት ተለይተው የታወቁ ችግሮችን ለመፍታት ኘሮጀክቶች /እያንዳንዳቸው/ ራሳቸውን ችለው ሊታቀዱ፣ ፋይናንስ ሊደረጉ፣ ሊተገበሩ፣ ውጤታቸውና ስኬታቸው ሊለካ እንደሚችል የፅሁፍ ማስረጃዎችና በተግባር የተገኙ ተሞክሮዎች ያስገነዝባሉ፡፡ ሥርዓቱን ውጤታማና ስኬታማ በሆነ አግባብ ተፈፃሚ ለማድረግ የተሟሉ የማስፈፀሚያ መሣሪያዎች/መመሪያዎች ተጠንተውና ተዘጋጅተው ሥራ ላይ ሊውሉ ይገባል፡፡ በአገራችን የልማት ኘሮጀክቶችን ሥርዓትና የሥርዓቱን ማስፈፀሚያ ሜቴዶሎጂዎች ከማጥናት፣ ከማዘጋጀትና በሥራ ላይ እንዲውሉ በማድረግ ውስን የአገር ሀብት ውጤታማና ስኬታማ በሆኑ የልማት አማራጮች ላይ ተመድቦ ተፈፃሚ እንዲሆን ከማስቻል አኳያ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በተጨባጭ ሊታዩ የሚችሉ በርካታ ጥረቶችን አድርጓል፡፡ ከነዚህ ጥረቶች መካከል ዋና ዋናዎቹ፡-

  1. ጥናቱ የተጠናቀቀና በሥራ ላይ እንዲውል ለሚኒስትሮች ምክር ቤትና ለብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት ርዕሳነ መስተዳደር ጽ/ቤቱች የቀረበ የልማት ኘሮጀክቶች አዘገጃጀት፣ አፀዳደቅና አፈፃጸም ሥርዓት ሰነድ፣
  2. ጥናቱና ዝግጀቱ ተጠናቅቆ ለፌዴራል መንግስት የሚመለከታቸው አስፈፃሚ መ/ቤቶችና ለብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮዎች በበቂ ኮፒዎች የተሰራጨና ሥራ ላይ የዋለ የልማት  ኘሮጀክቶች ዝግጅት መመሪያ (Guidelines for the Preparation of Public Sector Projects)፣
  3. ጥናቱና ዝግጀቱ ተጠናቅቆ ለፌዴራል መንግስት የሚመለከታቸው አስፈፃሚ መ/ቤቶችና ለብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮዎች በበቂ ኮፒዎች የተሰራጨና ሥራ ላይ የዋለ ክፍለ ኢኮኖሚን መሠረት በማድረግ የኘሮጀክት ዝግጅት ልዩ ባህሪያትን የሚያካትት ደጋፊ ናሙና ቴክኒካዊ መሣሪያ (Sample Supplementary Technical Tool)፣
  4. የመንግስት ሀብት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ውጤታማ የኢኮኖሚ ዕድገትና ልማትን በሚያስገኙ የልማት አማራጮች ላይ ለመመደብና ሥራ ላይ ለማዋል ቁልፍ መሣሪያ የሆነና በተለያዩ ጊዜያት ተገምግሞ ሥራ ላይ የዋለ የብሔራዊ ኢኮኖሚ መመዘኛዎችና የመለወጫ ማመጣጠኛዎች ሰነድ (National Economic Parameters And Conversion Factors For Ethiopia) /ይህ ሰነድ እንደ አውሮፖውያን አቆጣጠር በ1981 ዓ.ም ተዘጋጅቶ ሥራ ላይ እንዲውል የተደረገ ሲሆን በ1989 ለመጀመሪያ ጊዜ፣ በ1998 ለሁለተኛ ጊዜ፣ በ2007 ለሶስተኛ ጊዜ ክለሳዎች (Revision) ተደርገውለታል፣ሶስተኛው የክለሳ ሥራ የተጠናቀቀው በአለፈው ታህሳስ መጨረሻ 2007 ሲሆን የክለሳ ሰነዱ በህትመት ሂደት ላይ የሚገኝ/፣
  5. ጥናቱና ዝግጅቱ ተጠናቅቆ በህትመት ሂደት ላይ የሚገኝ የልማት ኘሮጀክቶች ክትትልና ግምገማ መመሪያ ናቸው፡፡