የታክስ አወሳሰን
በአዋጅ ቁጥር 286/2002 እና በደንብ ቁጥር 78/2002 መሰረት የታክስ ገቢ የሚባለው ሌላ የሚቀረጡና የሚከፈሉ ነገሮች በሙሉ ተቀንሰው ቀሪ የሆነውና የሚቀረጠው የእቃ ገቢ ነው፡፡
የገቢ ግብር
የገቢ ግብር የሚያጠቃልለው የቅጥር ገቢ፣ የንግድና የግል እንቅስቃሴዎች፣ ኗሪ ባልሆኑ ሰዎች አዳዲስ የፈጠራ እንቅስቃሴዎች፣ ተንቀሳቃሽ ንብረቶችንና የመሳሰሉትን ነው፡፡ ማንኛውም ቅጥር ከደሞዙ ላይ ይህንን ግብር መክፈል አለበት፡፡
የኮርፖሬት ታክስ
የኮርፖሬት ታክስ መጠኑ ኮርፖሬቱ በሰራው ስራ ላይ ታክስ ከሚደረጉ የኮርፖሬቱ ኘሮጀክቶች 30% ነው፡፡
የተርንኦቨር ታክስ
ይህ ደግሞ ዓመታዊ ገቢያቸው ከ500,000 ብር በታች የሆኑ እና የተጨማሪ ዕሴት ታክስ የማይመለከታቸውን ያጠቃልላል፡፡ የሚሰላውም በአጠቃላይ ከተገኘው ገቢ 2 መቶውን በመውሰድ ነው፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ
የተጨማሪ እሴት ታክስ ዓመታዊ ገቢያቸው ከ500,000 ብር በላይ የሆኑ የግብር ከፋዮች በሚያደርጓቸው በእያንዳንዱ ታክስ የሚያስከፍል በተደነገገ የንግድ ልውውጥ ከደንበኞቻቸው 15% ታክስ እንዲሰበሰቡ እና ለመንግስት ገቢ እንዲያደርጉ በመንግስት የተወሰነ የታክስ ዓይነት ነው፡፡
ኤክሳይዝ ታክስ
ሀገር ውስጥ የተመረቱ ምርቶች ላይ የሚደረግ የታክስ አይነት ነው፡፡
ከነዚህ ሌላ ከውጪ የሚገቡ እቃዎች ላይ የባለቤትነትና የሼርሆልደሮች ላይ የሚደረግ ታክሶች ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ፣ ሮያሊቲ ታክስና ዲቪደንድ ታክስ ናቸው፡፡