1. ሀገራዊ ራዕይ
በሕዝብ ተሳትፎና በሕዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ፣ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትና መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፣ ማኀበራዊ ፍትህ የነገሰባት፣ ከድህነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ ያላት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው፡፡
2. የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ እሴቶች፣ ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮችና ስትራቴጂያዊ ግቦች
2.1 ተልዕኮ
የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ የልማት ፖሊሲዎችን መቅረፅ፣ የልማት እቅድና በጀት ማዘጋጀት፣ ሀብት ማሰባሰብና ማስተዳደር፣ ዘመናዊ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተጠያቂነት ያለው የመንግስት ፋይናንስና ንብረት አስተዳደርና ቁጥጥር ሥርዓት ማስፈን፡፡
2.2 ራዕይ
ለፈጣን፣ ዘላቂና ፍትሀዊ የኢኮኖሚ እድገት ብቁና መሪ ተቋም መሆን፣
2.3 እሴቶች
● ሕግ፣ ደንብና መመሪያ ለውጤት
● በቡድን ስራን የመስራት ባህል
● የመማርና የመለወጥ ተነሳሽነት
● የተገልጋዮችን እርካታ ማዕከል ያደረገ የግብ ስኬት
2.4 ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች
● የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደርና ቁጥጥር
● ሀብት ማሰባሰብና ውጤታማ አጠቃቀም
● የኢኮኖሚ አመራርና አስተዳደር
2.5 ስትራቴጂክ ግቦች፣
ሀ. አገራዊ ዕይታ
● ኢኮኖሚውን ፈጣን፣ ዘላቂና ፍትሀዊነት ባለው መልኩ ማሳደግ
● የማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደርን ማሻሻል
● የልማት ሀብት አቅርቦትን ማሳደግ
● የሥነ-ህዝብ ባህሪያትን ከኢኮኖሚ አቅም ጋር ማጣጣም
● የመረጃ አቅርቦት፣ ስርጭትና ኮሙኒኬሽንን ማጎልበት
● የልማት አጋርነትና ትስስር ማሳደግ
ለ. የሀብት ዕይታ
● የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነትን ማሻሻል
● የሀብት ፍሰትን ማሻሻል
ሐ. የአሠራር ሥርዓት ዕይታ
● የመንግስት ፋይናንስና የውስጥ ኦዲት የአሠራር ሥርዓትን ማሻሻል
● የክትትልና ግምገማ ሥርዓትን ማጠናከር
● የልማት ዕቅድና የበጀት አሰራር ሥርዓትን ማሻሻል
● የመረጃ ልውውጥ ሥርዓትን ማሻሻል
መ. የመማማርና ዕድገት ዕይት
● የሰው ኃይል ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከትን ማሳደግ
● የሥራ አካባቢ ምቹነትን ማሻሻል
● የአመራርና የመወሰን ብቃትን ማሻሻል
● የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አቅርቦትን ማሳደግ
3. የመ/ቤቱ የሕግ አቋም
የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣ አዋጅ ቁጥር 691/2003 የተቋቋመ መ/ቤት ነው፡፡
መ/ቤቱ በአዋጅ በተሠጠው ሥልጣን መሠረት የልማት ፖሊሲና ዕቅድ የመቅረፅና አፈፃፀሙን የመከታተል፤ በዘላቂ ጥቅም ላይ የተመሠረተ የውጭ ኢኮኖሚ ትብብር ሥርዓትና አስተዳደር የመዘርጋትና ቀልጣፋና ውጤታማ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር መመሥረት ላይ አተኩሮ የሚሰራ ነው፡፡
እነዚህንም ተግባራዊ ለማድረግ መ/ቤቱ በአንድ ሚኒስትርና በሦስት ሚኒስትር ዴኤታዎች የሚመራ ነው፡፡
የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መ/ቤት በፌዴራል መንግስት ሠራተኞች አዋጅ የሚተዳደር ሲሆን የደመወዝ፣ ደረጃ ዕድገት፣ ዝውውርና ድልድል፣ ህክምና ልዩ ልዩ ፈቃዶች፣ ጡረታና ካሣ የመሳሰሉት ጉዳዮች በአዋጁ መሠረት ተፈፃሚ የሚሆኑ ናቸው፡፡