የኢትዮጵያ ማዕከላዊ እስታትስቲክስ ኤጀንሲ በ1981 ዓ.ም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒሰትር በበላይነት እየተመራ እንዲሰራ በአዋጅ ተቋቁሟል ፡የኤጀንሲው ዓላማም በሃገሪቱ የሚከነወኑ የህዝብ ቆጠራ በበላይነት መምራትና የተለያዩ ናሙናዎችን ማከናወን ነው፡፡ በመሆኑም የሃገሪቱ የመረጃ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል፡፡ ኤጀንሲው ይህንን ስራውን በብቃት ለማከናወን በሃያ አምስት የ/ቅ/ጽ/ቤቶች በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የተዋቀረ ሲሆን፡ እነዚህም በአምቦ፡ በአርባ ምንጭ፡ አሰበ ተፈሪ፡ አሳይታ፡ አሶሳ፡ አዋሳ፡ ባህር ዳር፡ ደብረ ብርሃን፡ ደሴ፡ ድሬደዋ፡ ጋምቤላ፡ ጎባ፡ ጎንደር፡ ሀረር፡ ሆሳዕና፡ እንደ ሥላሴ፡ ጂጂጋ፡ ጂማ፡ መቀሌ፡ ሚዛን ተፈሪ፡ነገሌ ቦረና፡ ነቀምትና ሶዶ ናቸው፡፡