Back

ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ስልጠና ተሰጠ

የገንዘብ ሚኒስቴር ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት በፊዝካል ፖሊሲ፣ በብድርና ዕርዳታ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

በገንዘብ ሚኒስቴር የፊዝካል ፖሊሲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መዝገቡ አመሀ እንደተናገሩት  ፊዝካል ፖሊሲ አንዱ የማክሮ ኢኮኖሚ መተግባሪያ መሳሪያ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የፊዝካል ፖሊሲ  በተመለከተ ማለትም ሰመንግስት ብድር፣ ገቢ እና ወጪዎች በተመለከተ ለምክር ቤት አባላት ሲፊ ማብራራያ ሰጥተዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አሁን እየታዩ ስላሉ የገቢ ምንጮች ማለትም ስለታክስ አሰባሰብ፣ታክስ ስላለሆኑ ገቢዎች እና የብድር ሁኔታም ገለፃ አድረገዋል፡፡

ሀገሪቱ እየሰበሰበችው ያለው ገቢ ከአጠቃላይ የምርት ዕድገቱ ጋር ሲነጻጸር 12 በመቶ ያላለፈ በመሆኑ መንግስት በብድርና ዕርዳታ የበጀት ጉደለቱን ሲሸፈን መቆየቱን ተናግረዋል፡፡የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን በማሻሻል እንዲሁም የታክስ ስወራን በመከላከል የሚሰበሰበውን ገቢ ማሳደግ እንደሚቻልም ገልፀዋል፡፡ ይህን ለማድረግም በመስሪያ ቤቶች በኩል በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ብድርና ዕርዳትን ባህሪያት፣ዓይነቶች፣ጠቀሜታና ተግዳሮቶች ላይ በገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስታት ትብብር ኃላፊ የሆኑት አቶ ኮከብ ምስራቅ ለምክር ቤቱ አባለት ገለፃ አድርገዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባለት ከተደረገው ገለፃ በኋላ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡ለአብነትም ስለ እዳ ጫና፣ በመንግስት ዋስትና ተሰጥቷቸው ብድር ስለወሰዱ የመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ በብድር ስለሚሰሩ ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት፣ሰለ ፕሮጀክቶች ክትትል፣የተገኙ ብድሮች ለተገቢው አላማ ስለመዋላቸውና ሌሎችም ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡

ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አዳማሱ ነበበ እንዳሉት የብድር ጫና የመጣው በአግባቡ የአዋጭነት ጥናት ሳይሰራላቸው ወደ ስራ በሚገቡ ፕሮጀክቶችና በደካማ የክትትል ስርዓት ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህን ችግር ለመከላከል ላልተወሰነ ጊዜ የንግድ ብድር (Commercial loan) እንዲቆም እንዲቆም ተደረጓል፡፡የንግድ ብድር የሚወስዱ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ከዚህ ቀደም በራሳቸው ተደራድረው ጨርሰው የገንዘብ ሚኒስቴር ዋስትና ብቻ ይሰጥ የነበረ መሆኑን ያስታወሱት ሚንስትር ዴኤታው ይህን ችግር ለመቅረፍ የሚያግዝ የብድር መመሪያ በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡የሚቀርቡ የብድር ጥያቄዎች የአዋጭነት ጥናታቸው በአጥጋቢ ሁኔታ ተሰርቶ፤ከዚህ በፊት ያላቸው አፈፃፀም ታይቶ በቴክኒክ ኮሚቴ ሲፀድቅ ብቻ ብድሩ እንደሚፈቀድም ገልፀዋል፡፡

በስልጠናው መዝጊያ ላይ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ እንዳሉት በንግድ ብድሮች የሚሰሩ ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናታቸውን አስተማማኝነት እና ዕዳቸውን መመለስ መቻል አለመቻላቸው መታየት እንዳለባቸው አሳሰበዋል፡፡ከአሰራር ውጭ ሀላፊነቱን ያጎደለም ተጠያቂ መሆን ይኖርበታል ሲሉም ተናግረዋል፡፡የቀላል ብድሮችንም ውጤታማነትና ፍትሀዊነት የሚመለከታቸው አካላት በጋራ ሊሰሩበት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡


News Archive News Archive