የመንግስትን ሀብት ውጤታማ በሆነ መንገድ ሥራ ላይ ለማዋል የመንግስት ፋይናንስና ግዥ አስተዳደር ህጎችን ጠንቅቆ መረዳት እንደሚገባ ተገለፀ
የመንግስትን ሀብት ውጤታማ በሆነ መንገድ ሥራ ላይ ለማዋል የመንግስት ፋይናንስና ግዥ አስተዳደር ህጎችን ጠንቅቆ መረዳት እንደሚገባ ተገለፀ
የመንግስትን ሀብት በቁጠባ፣ በቅልጥፍና እና ውጤታማ በሆነ መንገድ ሥራ ላይ ለማዋል የመንግስት ፋይናንስና ግዥ አስተዳደር ህጎችን ጠንቅቆ መረዳት እንደሚገባ የገንዘብ ሚኒስትሩ ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ ከ45 የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም የፋይናንስ የግዥ እና የውስጥ ኦዲት ኃላፊዎች ጋር በገንዘብ ሚኒስቴር በተደረገው ምክክር መክፈቻ ላይ ገለፁ፡፡ ሚኒስትሩ አክለውም ዩኒቨርሲቲዎች ቁጥራቸው በማየሉ፣ የሚያስተናግዷቸው ተማሪዎችም በርካታ በመሆናቸው እንዲሁም የሚጠቀሙት የመንግስት ሀብት በዚያው ልክ በመጨመሩ በፋይናንስና ግዥ ስርዓቱ ላይ ሥልጠና መስጠት እንዳስፈለገ ገልፀው የበላይ አመራሮችና የፋይናንስ ባለሙያዎችም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
የመንግስት ፋይናንስን በማስተዳደር፣ በመምራትና በመቆጣጠር ረገድ አጠቃላይ ኃላፊነት የተጣለው በመንግስት መ/ቤቶች የበላይ ኃላፊዎች ላይ እንደሆነም ተወስቷል፡፡ ኃላፊዎች ለመ/ቤታቸው የተፈቀደው በጀት ህግና መመሪያ በሚያዘው መሰረት ብቻ ጥቅም ላይ መዋሉን ማረጋገጥ እንዳለባቸውናም ተብራርቷል፡፡
የኢትዮጵያ ፊሲካል ፖሊሲ የሀገሪቱን የልማት ዓላማዎች ለማስፈፀም በመንግስት ገቢ (የውጭ እርዳታን ጨምሮ) ወጪና ብድር አስተዳደር አማካኝነት ሥራ ላይ የሚውል ቁልፍ መሣሪያ እንደመሆኑ ይህን ዓላማ ለማስፈፀምና ውጤታማ ለማድረግ ደግሞ ብቁና ጠንካራ አስፈፃሚ አካላትን መገንባት አስፈላጊ እንደሆነም ገለፃ ተደርጓል፡፡
News Archive
-
የገንዘብና ሚኒስቴር በቀዳሚው የ100 ቀናት ዕቅድ አፈፃፀምና በሁለተኛው ዕቅድ ዙሪያ መከረ
-
የመንግስትን ሀብት ውጤታማ በሆነ መንገድ ሥራ ላይ ለማዋል የመንግስት ፋይናንስና ግዥ አስተዳደር ህጎችን ጠንቅቆ መረዳት እንደሚገባ ተገለፀ
-
በመንግስት የፋይናንስ አስተዳደርን አስመልክቶ ምክክር ተካሄደ
-
ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ስልጠና ተሰጠ
-
በመንግስትና በግል አጋርነት የሚሰሩ የፀሐይ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ይፋ ሆኑ
-
ኢትዮጵያና የአፍሪካ ልማት ባንክ ለተቀናጀ የግብርና-ኢንዱስትሪ ፓርኮች ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል የ15 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረሙ
-
Ethiopia is committed to support Basic Service delivery and system strengthening programs
-
Ethiopia Signed Financing Agreement with the World Bank
-
Ethiopia Signed Financing Agreement with the World Bank
-
Agreement Signed to Increase the Productivity and Competitiveness of the Livestock Sector
-
Ethiopia and Development Partners holding discussion on Basic Service Programs
-
Ethiopia Economy Expected to Move toward a more sustainable path