Back

ኢትዮጵያ በ2012 በጀት ዓመት ከበይነ-መንግሥታዊ ተቋማት (Multilateral) እና ከመንግስታት ትብብር (Bilateral) በብድር እና እርዳታ 106.8 ቢሊዮን ብር በግኝት እንዲሁም በፍሰት (Disbursement)142.2 ቢሊዮን ብር የልማት ድጋፍ አገኘች፡፡

በ2012 በጀት ዓመት ከመልቲላተራልና ባይላተራል ምንጮች የተገኘና የፈሰሰ የውጭ ሀብት

ሀገራችን ከሁለት ዋና ዋና ምንጮች የውጭ ብድርና እርዳታ ታገኛለች፡፡ አንደኛው ከበይነመንግሥታዊ ተቋማት (Multilateral) ምንጭ ሲሆን በዚህም ውስጥ የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ተቋማት (የዓለም ባንክ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ወዘተ) የአውሮፓ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች ይካተታሉ፡፡ ሁለተኛው የመንግስታት ትብብር (Bilateral) ሲሆን በዚህ ውስጥ ደግሞ ቻይናን ጨምሮ ለአገራችን የልማት ፕሮግራመች ማስፈጸሚያ ድጋፍ የሚያደርጉ የተለያይ የልማት አጋር መንግሥታት ይካተታሉ፡፡ በዚህ መሠረት በ2012 በጀት ዓመት ከዚህ በታች ተዘርዝሮ የቀረበው የብድርና ርዳታ ግኝትና1 ፍሰት ተመዝግቧል፡፡

 1. ግኝት1
 • ከመልቲላተራል ምንጮች በ2012 በጀት ዓመት ውስጥ፡-
 • በብድር ብር 18.761 ቢሊዮን2
 • በእርዳታ ብር 39.774 ቢሊዮን
 • በድምሩ ብር 58.535 ቢሊዮን አዲስ ብድርና እርዳታ ተገኝቷል፡፡

 

 • በ2012 በጀት ዓመት ከመንግሥታት ትብብር /ባይላተራል፣ ምንጮች፡-
 • በብድር ብር 18.619 ቢሊዮን
 • በእርዳታ ብር 29.721 ቢሊዮን
 • በድምሩ ብር 48.34 ቢሊዮን አዲስ ብድርና እርዳታ ተገኝቷል፡፡

 

 • በ2012 በጀት ዓመት ውስጥ ከሁለቱም ምንጮች፡-
 •   በብድር ብር 37.38 ቢሊዮን
 •   በእርዳታ ብር 69.495 ቢሊዮን
 • በድምሩ ብር 106.875 ቢሊዮን /የዕቅዱን 81.3%/ አዲስ ብድርና እርዳታ  ተገኝቷል፡፡
  1. ግኝት የሚባለው በተፈጸሙ ስምምቶች መሠረት ቃል የተገባና የታቀዱ ሥራዎችን ለማስፈጸም ከ3-10 ባሉ ቀጣይ ዓመታት ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ የሚፈስ ገንዘብ ነው፡፡

 

 1. ፍሰት
 • በ2012 በጀት ዓመት ለፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ
 • ከመልቲላተራል ምንጮች፡-
 • በብድር ብር 50.954 ቢሊዮን
 • በእርዳታ ብር 43.774 ቢሊዮን
 • ከመልቲላተራል ምንጮች በድምሩ ብር 94.728 ቢሊዮን የውጭ ሀብት ፍሰት ተገኝቷል፡፡

 

 • በሌላ በኩል ከመንግስታት /ባይላተራል/ ምንጮች፡-
 • ከብድር ብር 16.084 ቢሊዮን
 • ከእርዳታ ብር 31.485 ቢሊዮን
 • ከዚህ ምንጭ በጠቅላላ ብር 47.569 ቢሊዮን የውጭ ሀብት ፍሰት ተመዝግቧል፡፡
 • በአጠቃላይ በ2012 በጀት ዓመት ከሁለቱም ምንጮች፡-
 • በብድር ብር 67.038 ቢሊዮን
 • በእርዳታ ብር 75.259 ቢሊዮን
 • ከሁለቱም ምንጮች በበጀት ዓመቱ በድምሩ ብር 142.297 ቢሊዮን /የዕቅዱ 92.85%/ ፍሰት የተመዘገበ ሲሆን ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው የብድርና እርዳታ ፍሰት ብር 115.0012 ቢሊዮን ጋር ሲነፃፀር በ27.296 ቢሊዮን ብር ወይም በ23.73 ከመቶ ከፍ ያለ ነው፡
  •  

2ስሌቱ የተሰራው የ2011 አማካይ የምንዛሪ ተመን 1 ዶላር = 28.09 ብር፣ የ2012 አማካይ የምንዛሪ ተመን 1 ዶላር = 32.23 ብር ሆኖ ነው፡፡

3ፍስት በገንዘብ፣ በዓይነት /በእህል፣ በመድኃኒት፣ በማሽነሪ ወዘተ/ እና በቴክኒክ ድጋፍ መልክ ወደ አገር ውስጥ የሚገባ ሲሆን የሁሉም ዋጋ በገንዘብ ተተምኖ የተቀመጠ ነው፡፡  


News Archive News Archive