የሂዩማን ካፒታል ኦፕሬሽን የ2018 ዓመታዊ የስራ ዕቅድና በጀት ዝግጅት በተመለከተ ከፌዴራል እና ከክልሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ

By: Yonas M. | Published: June 30, 2025

ሰኔ 23/2017 ዓ.ም -  በመንግስት እና በልማት አጋሮቸ የፋይናንስ ድጋፍ ከ2016 ዓ.ም እስከ 2020 ዓ.ም  የበጀት ዓመት  የሚካሄደው የሂዩማን ካፒታል ኦፕሬሽን ( HCO) የ2018 በጀት አመት ዕቅድ እና በጀት ዝግጅት በአዳማ ከተማ መካሄድ ጀመረ፡፡

ከዝግጅቱ ጋር በተያያዘ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት  በገንዘብ ሚኒስቴር የቻናል አንድ ፕሮግራሞች ማሰተባበሪያ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደጉ ላቀው የእቅድና በጀት ዝግጅቱ ዋነኛ  ዓላማ በተለይም ሂዩማን ካፒታል ኦፕሬሽን ( HCO)  ሚተገብሩ የፌዴራል፤ የክልልና የወረዳዎች ሴክተር ሀላፊዎችና ባለሙያዎች እቅዱን ለመተግበር በሚያስችል ሁኔታ በጥራት እና በተሟላ ይዘት  እንዲዘጋጅ ያሳሰቡ ሰሆን ተሳታፊዎችም በሙሉ አቅማችው ተገቢውን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ አስገንዝበዋል፡፡

የኦፕሬሽኑ ዋና አላማ በተመረጡ ወረዳዎች ላይ የትምህርት አቀባበልና የህጻናት መቀንጨር ችግሮችን መፍታት ስሆን ከልማት አጋሮች የሚገኘው ፈንድ የሚለቀቀውም የገንዘብ ፍሰት ዉጤት አመልካቾችን አፈጻጸም መሰረት ያደረገ ነው፡፡ይህን  ማለት ወረዳዎችና ፈጻሚ አካላት በእቅዱ መሰረት ስራ ተሰርቶ ውጤት መገኘቱ ስረጋገጥ ነው፡፡በተጨማሪም ኦፕሬሽኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመሰረታዊ አገግሎት አቅርቦት እና የተጠያቂነትን ስርዓት ማጠናከርን ያካትታል፡፡

ከዝግጅቱ የሚጠበቀው ውጤት  በፌዴራል፣ በክልል እና በወረዳ የተቀናጄ  የመልቲ_ክተር ዓመታዊ  እቅድና በጀት ይሆናል፡፡

በዝግጅቱ ላይ ከፌዴራል፣ ከክልሎች እና በፕሮግራሙ ከታቀፉ ወረዳዎች የተወጣጡ ከ600 መቶ በላይየሚደርሱ የስራ ሃላፊዎቸ እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

 

437 Views