የዛሬው የገንዘብ ሚኒስቴር ከአንድ መቶ አመት በፊት ጥቅምት 14/1900 ዓ.ም. በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመነ መንግስት “የገንዘብና የጓዳ ሚኒስቴር” በሚል መሰረቱን ጥሎ የተለያዩ ታሪካዊ ሂደቶችን በማለፍ ለረጅም ዓመታት ተግባሩን እያከናወነ ለዛሬው ዕለት ደርሷል፡፡
መ/ቤቱ የሀገሪቱን የልማት እቅድ መቀመር፣ በጀት ማዘጋጀት ማስፀደቅና ማስተዳደር፣ የእቅድና በጀት አፈፃፀምን መከጻጸልና መገምገም እንዲሁም ፈጣንና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የተዘጋጁትን ዕቅዶች እውን ለማድረግ የአገር ውስጥ ፋይናንስ ግኝትን ማጎልበት እንዲሁም የውጭ ሀብት የማሰባሰብና በስራ ላይ በአግባቡ እንዲውል የማድረግ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ለፈጣን ኢኮኖሚ ዕድገት የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ መኖር አስፈላጊ እንደመሆኑ በማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲና ማኔጅመንት በኩልም የራሱን ድርሻ በመወጣት ላይ ይጀኛል፡፡
ኢትዮጵያ አሁንም ከድህነት ያልወጣች ቢሆንም መንግስት በየጊዜው በቀየሳቸው ፍሬያማ ፖሊሲዎች አጋዥነት በዋናነት በህዝብና በመንግስት የጋራ ርብርብ እንዲሁም በልማት ተባባሪ አገሮችና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ድጋፍ መሰረተ ልማት (መንገድ፣ ኀይል ማመንጫ፣ ቴሌኮሙኒኬሽን)፣ የሰው ኀይል ልማት (ትምህርት፣ ጤና፣ መጠጥ ዉኀ)፣ የዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ሥርዓት ግንባት እየተስፋፋና እየተጠናከረ ይገኛል፡፡ ዕንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ በሚሰጥ የተጠናከረ የኤክስቴንሽን አግልግሎት ገበያ መር የግብርና ልማቱም ውጤት እያሳየ ይገኛል፡፡ በጥሬ ገንዘብና በንብረት ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮችን እያፈራን ነው፡፡ ለተከታታይ አመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሁለት አሀዝ/double digit/ ዕድገት ማስመዝገቡ ለዕድገት ተስፋ ሰጪ ምልክት መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
አገራዊ ራእይ
“በህዝብ ተሳትፎና መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ዲሞክራሲያዊ ስርአትና መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፣ ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት፣ ከድህነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ ያላት፣ ኢትዮዽያን እውን ማድረግ፣”