በአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም መሰረት የመንግስት የልማት ድርጅቶች የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ተገመገመ

March 9, 2021

የአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብር ዋኛ አካል የሆነው የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ውጤታማነት ለማሻሻል ፣ ተወዳዳሪነታቸውን ለማጎልበት እና የአገልግሎቶት አሰጣጣቸውን ቀልጣፋ እንዲሆኑ ለመደገፍ ያተኮረ ለአምስት ቀናት የሚቆይ ውይይት ተጀመረ፡፡

በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ስር በሰባት ዘርፎች ማለትም በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ፣ በግብርና እና አግሮ ኢንዱስትሪ፣ በአምራች ኢንዱስትሪ እና ኢንጅነሪንግ፣ የንግድ እና የአገልግሎት ዘርፍ፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የኮመኒኬሽን እና የኮንስትራክሽን ስር ተመድበው የሚገኙ የመንግስት የልማት ድርጅቶች በ2013 በጀት አመት በመጀመሪያው አጋማሽ የነበራቸውን የስራ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ለሁሉም የልማት ድርጅቶች የኦዲት ሪፖርት ላይ የተሰጡ የማሻሻያ ሀሳቦችን ተግባራዊንት እንዲያረጋግጡ የግምገማው ትከረት ሰጥቷል፡፡

ውይይቱ የተመራው በገንዘብ ሚኒስትር በክቡር አህመድ ሽዴ ሲሆን፣ መንግሰት የልማት ድርጅቶቹን ለመደገፍ የቴክኒክ ኮሚቴዎቸን አዋቅሮ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰው በተለይም ሁሉም የልማት ድርጅቶች ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደር እና ሂሳብ አያያዝ ስርዓት ተከትለው እንዲተገብሩ በመደረጉ የአሰራር መሻሻሎች እየተገኙ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

ሚኒስትሩ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን የዕዳ መጠን ዘርዝሮ በማጥናትና የመክፈል አቅማቸውን ከግምት ውስጥ በማሰገባት የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን የዕዳ ጫና በማቃለል እና ውጤታማ ሆነው እንዲዘልቁ ለማስቻል የሚያግዝ የእዳና ሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን እንዲቋቋም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተወስኖ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡

የመንግሰት ልማት ድርጅቶች ለሀገር ልማትና እድገት ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦም እንዲያበረክቱ መንግስት የተለያዩ የፖሊሲ ማሻሻያዎች በመቅረፅ እና የአሰራር ስርዓቶችን በመንደፍ ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

የካቲት 8/2013 ዓ.ም የተካሄደው ውይይት በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮ-ቴሌኮም የስድስት ወራት የስራ አፈጻጻም ግምገማ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡

1599 Views