በክቡር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራው የልኡካን ቡድን ከሳውዲ ባለስልጣናት ጋር መከረ፡፡

Jan. 28, 2022

በገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራው የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን ከሳውዲ አረቢያ የንጉስ ሰልማን የሰብአዊ እርዳታ ማእከል የበላይ ሀላፊ ከክቡር ዶ/ር አብዱላህ አልራቢሀ ጋር በሁለቱ ሀገራት የጋራ ሰብአዊና የእርዳታ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ በተጨማሪም ከሳውዲ ልማት ፈንድ ስራ አስኪያጅ ከክቡር ሱልጣን አልማርሻድ ጋር ተገናኝተው የተወያዩ ሲሆን በሳውዲ ልማት ፈንድ የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ የሚያካሄዱትን የልማት ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ያሉበትን ሁኔታ በጋራ ገምግመዋል፡፡

ክቡር አቶ አህመድ በሳውዲ ልማት ፈንድ የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የልማት ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች በመሰረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታና ዘላቂ ልማትን ለማምጣት በሚደረገው ጥረት በሀገሪቱ ማህበራዊ አገልግሎትና በኢኮኖሚ እድገት ላይ አዎንታ አስተዋጾኦ እንዳላቸው አመልከተው ሳውዲ አረቢያ በሰብአዊ እርዳታና በኢኮኖሚ ልማት ለምታደርገው አስሰተዋጽኦ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

844 Views