ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በገንዘብ ሚኒስቴር ተከበረ
Oct. 16, 2023
ጥቅምት 5/2016- በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረው 16ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለኅብረ ብሐራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው!” በሚል መሪ መልእክት የገንዘብ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በተገኙበት ተከበረ፡፡
የሰንደቅ ዓላማ አከባበር ላይ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ሰንደቅ ዓላማችን የአንድነታችና የነፃነታችን ተምሳሌት፣የአገር ሉአላዊነት መገለጫና የህብረ-ብሄራዊ አንድነታችንም ምልክት ነው ብለዋል፡፡
በዓሉን ስናከብር ሀገራችን የጣለችብንን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣትና ለሀገሪቱ መፅናት ዋጋ የከፈሉ ዜጎችን በማክበር መሆን አለበትም ብለዋል፡፡
የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከባበሩ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞችና አመራሮች በተገኙበት የኢትዮጵያን ህዝብ መዝሙር በጋራ በመዘመርና ሰንደቅ ዓላማን በመስቀል ተጠናቋል፡፡