አዲስ በሚገነባው ግዙፍ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የግንባታ ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ
March 9, 2021
በአዲስ አበባ ዙሪያ አዲስ በሚገነባው ግዙፍ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ቅድመ ዝግጅት ላይ በገንዘብ ሚኒስቴር ውይይት ተካሄደ፡፡
የገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ ከኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ከክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ከአቶ ተወልደ ገ/ማሪያም ጋር በኢትዮጵያ ሁለተኛው ሜጋ ፕሮጀክት በሆነው አዲሱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቅድመ ዝግጅት ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂደዋል፡፡
ውይይቱ በተካሄደበት ወቅት አዲሱ ፕሮጀክት የኢትዮጵያ የኤርፖርት አገልግሎትን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሻግር ተመላክቷል፡፡ በተጨማሪም በዕቅድ በተያዙ አምስት የአውሮፕላን ማረፊያዎች እና ተርሚናሎችን የማስፋፋት ስራዎች መሰናዶ ላይ የጋራ መግባባት ተደርሷል፡፡
ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን ኢትዮጵያን የአየር ትራንስፖርት ተጓዦች እና የካርጎ መናኸሪያ በመሆን የላቀ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል፡፡በተጨማሪም ለኢትዮጰያ ዘላቂ ልማትና እድገት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል፡፡