ኢትዮጵያና ቻይና የ161 ሚሊዮን ብር የአስቸኳይ ምግብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ
Feb. 7, 2023
ጥር 30/2015 አዲስ አበበ - ኢትዮጵያና ቻይና የ161 ሚሊዮን ብር የአስቸኳይ ምግብ ድጋፍ ስምምነት በገንዘብ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተፈራረሙ፡፡
የፋይናንስ ድጋፉ በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የሚውል ሲሆን በሀገሪቱ በግጭትና በተፈጥሮ አደጋዎች ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡
በስምምነቱ ወቅት በተካሄደው ውይይት በሁለቱ ሀገራት መካከል በሚካሄደው የኢኮኖሚ ትብብር በቀጣይ የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸውና ቻይና ለኢትዮጵያ የቀላል ባቡር ፕሮጀክት የምትሰጠውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተመልክቷል፡፡
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ትብብር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የኢኮኖሚና ንግድ አማካሪ ሚስተር ያንግ ዪሀንግ ተፈራርመዋል።