ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ የገንዘብ ሚኒስትር የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አምባሳደር እና የአፍሪካ ህብረት ቋሚ ተወካይ ክቡር መሃመድ ሳሌም አልራሺድን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

March 9, 2021

ውይይቱ የሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብርን በማጠናከር በተለይም ደግሞ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ባለሀብቶችና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ በማበረታታት ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል የንግድ፣ ቱሪዝም እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማጎልበት በሚቻልበት መንገድ ላይ የጋራ ምክክር አድርገዋል፡፡

725 Views