የሀዘን መግለጫ

Feb. 19, 2024

 

በገንዘብ ሚኒስቴር ከ1969 ዓ.ም ጀምሮ በዋና ፕሮቶኮልነት ተቋሙንና ሀገርን ላለፋት 47 ዓመታት ያገለገሉት አቶ ስዩም ከበደ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው የካቲት 9/2016 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡

አቶ ስዩም ከበደ ጡረታ ከወጡም በኋላ በኮንትራት ተቀጥረው በአጠቃላይ በተቋሙ ላለፋት 47 ዓመታት ሲያገለግሉ በታታሪነትና በቅንንት በውጤታማ ስራቸው የሚታወቁ ሲሆን ከመስሪያ ቤቱ የስራ ሀላፊዎችና ሰራተኛ ጋር ተግባብትው የሚሰሩ ተወዳጅ ባልደረባ ነበሩ፡፡

አቶ ስዩም ከበደ በ1945 ዓ.ም በቀድሞው አጠራር በሸዋ ክፍለ ሀገር በሰላሌ አውረጃ በደብረ ሊባኖስ ወረዳ እንደተወለዱ የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች በአቶ ስዩም ከበደ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን እየገለፁ፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸውና ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ይመኛሉ፡፡

1473 Views