የመስኖና ቆላማ አካባቢ፣ የውሃና ኢነርጂ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የ2016 የበጀት ስሚ መርሀግብር ተካሄደ

April 28, 2023

ሚያዚያ 20/2015 ዓም- በዛሬው ዕለት በነበረው የበጀት ስሚ መርሀግብር የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የ2016 የበጀት ዕቅድ በገንዘብ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ቀርቦ ተገምግሟል፡፡

የበጀት ድልድሉ የተሰራው ሀገራዊ ሁኔታውንና የተቋማቱን ተልዕኮ ግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነ የገለጹት የበጀት ስሚ ፕሮግራሙን የመሩት የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ፤ የተጀመሩ የውሃ ፕሮጀክቶችን በአግባቡ በመከታተል ማጠናቀቅ እንደሚገባ  እና መስኖን በተመለከተም አስፈላጊውን የአቅም ግንባታ ስራ በበጀት እንደሚደገፍ አመልክተዋል፡፡

በእያዳንዱ ተቋም የበጀት ዕቅድ ላይ በቂ ውይይት ከተካሄደ በኋላም የተመደበውን በጀት በቁጠባና በውጤታማነት በመጠቀም ተቋማቱ ተልዕኳቸውን በአግባቡ እንዲወጡና በተሰጣቸው ዝርዝር አስተያየት መሰረት በሁለት ቀናት ውስጥ የተስተካከለ የበጀት ዕቅዳቸውን ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ ዶ/ር ኢዮብ አቅጣጫ ሰተዋል፡፡

በመጨረሻም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት የ2016 በጀት ዝግጅታቸውን አቅርበዋል፡፡

1218 Views