የመንግስት የልማት ድርጅቶች የአንደኛ ሩብ አመት የሥራ አፈፃፀም እየተገመገመ ነው

Nov. 10, 2021

 

የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ተወዳዳሪነታቸውን ለማጎልበት እና የአገልግሎቶት አሰጣጣቸውን ቀልጣፋ እንዲሆን ለማስቻል ለአምስት ቀናት የሚቆይ ውይይት ተጀመረ፡፡

በዛሬው ዕለት የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን እና  የስኳር ኮርፓሬሽን የስራ ክንውን ቀርቧል፡፡ የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን በሩብ ዓመት አፈፃፀም ከምርት ሽያጭና ከሌሎች ገቢዎች በድምሩ ብር  ብር 643 ሚሊዮን ገቢ ማግኘቱ በግምገማው  ላይ ተጠቅሷል፡፡ ኮርፓሬሽኑ ባደረገው የሪፎርም ስራዎች የገበያ ስትራቴጂ መመሪያ በማዘጋጀት፣ የዋጋ ማስተካከያ በማድረግ እና የመሸጫ አውታሮችን የማስፋት ስራዎች መከናወናቸው የተጠቀሰ ሲሆን እነዚህ ዋና ዋና ተግባራ ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸውም በግምገማ መድረኩ ላይ ተገልጽዋል፡፡

የስኳር ልማት ኮርፓሬሽን  51,391 ቶን ስኳር በመሸጥ ከ1.14 ቢሊዮን ብር በላይ ማገኘት እንደቻለ በሪፖርቱ ላይ የተገለጸ ሲሆን ኮርፓሬሽኑ የውጪ ቅናሳ ተግባራዊ በማደረግ ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ከወጪ ለማዳን ችሏል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ መንግሰት የልማት ድርጅቶቹን ለመደገፍ የተለያዩ ስራዎች እያተከናወነ መሆኑን ገልጸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለልማት ድረጅቶቹ የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡  

የሰራ አፈጻጸም ግምገማውም በሚቀጥሉትም ቀናት ቀጥሎ የኢትዮጵየ አየር መንገድን ጨምሮ የሌሎች የመንግስት ልማት ድረጅቶች የስራ አፈጻተጸም ግምገማ እንደሚካሄድም ታወቋል፡፡

 

1765 Views