የሰሜን ዕዝ የተጠቃበት ጥቅምት 24 በገንዘብ ሚኒስቴር ታስቦ ዋለ
Nov. 3, 2021
የሰሜን ዕዝ በአሸባሪው የህወሀት ቡድን የተጠቃበት ጥቅምት 24 ‹‹ አልረሳውም! እኔም የኢትዮጵያ ሰራዊት ነኝ ›› በሚል መሪ ቃል ዛሬ ጥቅምት 24 2014 ዓ.ም የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በሚኒስቴሩ ቅጥር ጊቢ በተከናወነ ሥነስርአት ታስቦ ዋለ፡፡
በሥነስርአቱ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ እንዲሁም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን ‹‹ አልረሳውም! እኔም የኢትዮጵያ ሰራዊት ነኝ ›› በሚል መሪ ቃል አመራሩና ሰራተኛው ቀኝ እጅን በግራ ደረት ላይ በማኖር ጥቅምት 24 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ የሀገራቸውን ዳር ድንበር በማስጠበቅ ላይ በነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የተፈጸመው ጥቃት በአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ታስቧል፡፡
የሰራዊቱ አባላትን ለማስታወስም የሻማ ማብራት ስነስርአት የተከናወነ ሲሆን ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ተጠናቋል፡፡