የሰንደቅ ዓለማ ቀን በገንዘብ ሚኒስቴር ተከበረ
Published: Oct. 13, 2025
ጥቅምት 3/ 2018 ዓ.ም - 18ኛው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ህዳሴ!” በሚል መሪ መልዕክት የገንዘብ ሚኒስቴር አመራሮና ሰራተኞች በተገኙበት ተከበረ፡፡
በአከባበሩ ሥነ ሥርአት ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፋት የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው እንዳሉት ሰንደቅ ዓለማችን ዜጎቿ በተለያዩ ዓለማቀፍ መድረኮች ጭምር በኩራት የሚያውለበልቡትና ለሌሎችም ሀገራት የነፃነትና የኩራት ምልክት የሆነ ሰንደቅ ዓላማ ነው ብለዋል፡፡
ሚንስትር ዴኤታዋ አያይዘውም ብሄራዊ ሰንደቅ አላማችን የብሄራዊ አንድነታችንና ሉአላዊነታችን መገለጫ፣ የህብረ ብሄራዊነታችንና የአብሮነታችን ማሳያ፣ የአንድነታችን የጋራ አርማ፣ የነጻነታችንና የሉአላዊነታችን ህያው ምስክር ነው ብለዋል፡፡
ዘንድሮ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ሲከበረ ስለሰንደቅ ዓላማ ምንነት፣ ክብርና ትርጓሜ በተገቢው በመረዳት፣ ለሀገራችን ሉዓላዊነት፤ ነጻነት እና ለሰንደቃችን ክብር የተደረገውንና እየተደረገ ያለውን ተጋድሎ ዕውቅና በመስጠት የጋራ መግባባት መፍጠር፤ ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትንና እህትማማችነት በማጠናከር ብሄራዊ አንድነትን ማጽናት በሚል ዋና አላማ እየተከበረ ይገኛል፡፡