የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከልማት አጋሮች ጋር ውይይት አካሄደ

July 3, 2022

ሰኔ 24 / 2014 ዓ.ም የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሚደረገው ድጋፍ ላይ ከልማት አጋሮችን ጋር ምክክር አካሄደ፡፡

የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ኮሚሽኑ እስካሁን የሠራቸውን ተግባራትና በቀጣይ ስለሚያከናውናቸው ተግባራት ላይ ለልማት አጋሮች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ሰመሪታ ሰዋሰው በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ የተለያዩ የፖለቲካ፣ የአመለካከት ፣ የሀሳብ ልዩነትቶች ብሎም አለመገባባቶች በሰፊ የህዝብ ውይይቶች ሊፈቱ እንደሚገባ መንግስት በጽኑ ያምናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ሚኒስቴር ዴኤታዋ እንደገለፁት ሁሉንም ያሳተፈ ሀገራዊ ውይይት ማካሄድ በሀገሪቱ ላይ የተደቀኑ ፈተናዎችን ለመቋቋም እንደሚያስችል ተናግረው ስራውን የተቀናጀ እና ተቋማዊ ማድረግን ይጠይቃልም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ለኮሚሽኑ የሚደረጉ የልማት ድጋፎችን የትረስት ፈንድ በማቋቋም እንዲያስተባብር ውክልናም ሰጥቷል።

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በቀጣይ ለኮሚሽኑ በሀብት አሰባሰብ እና በፈንድ አስተዳደር ዙሪያ ድጋፍ ያደርጋልም ተብሏል፡፡

 

 

 

 

1886 Views