የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፋት ዓመታት ከነበረበት ችግር አገግሞ ለውጥ በማምጣት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

Nov. 12, 2021

 

ባንኩ በለውጥ ሂደት ላይ አንደሚገኝ የተገለጸው የባንኩ የ2014 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ለመገምገም በተደረገ ውይይት ላይ ነው፡፡

በውይይቱ ወቅት ባንኩ ትርፋማ ሆኖ መቀጠሉ፣ የታማሚ ብድር ምጣኔው እየቀነሰ መገኘቱ፣ ከዕቅድ ጋር ሲነጻጸር የብድር ተሰባሰቢው በተሻለ ደረጃ መፈጸሙ የተጠቀሰ ሲሆን የባንኩን ቢዝነስ ሞዴል ለማስተካከል እና የብድር አሰጣጥ ሥርዓቱ የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ማስተካከያ ማድረጉና የባንኩ የፋይናንስ ጤናማነት እየተሻሻለ መምጣቱም ተገልጿል፡፡

ውይይቱን የመሩት የገንዘብ ሚንስትሩ ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ ባንኩ ያስመዘገባቸው ውጤቶች ዘላቂነት እንዲኖራቸው ለማድረግ ተቋሙ ዘላቂ የገንዘብ ምንጭ እንዲኖረው፣ አሁንም የታማሚ ብደር ምጣኔውን እንዲቀንስ፣ የፕሮጀክቶች ክትትል እንዲጠናከር ፣ እንዲሁም ትርፋማነቱን ለማስቀጠል አዳዲስ የፋይናንስ አማራጮችን በማቅረብና የቅርንጫፍ አከፋፈቱን ፍትሀዊ በማድረግ ላይ የተጠነናከረ ስራ መስራት አለበት ብለዋል፡፡

1166 Views