የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገር ውስጥ ተወዳዳሪነት ከማሳደግ ባለፈ በምስራቅ አፍሪካ ያለውን የገበያ ድርሻ መጨመር እንደሚገባው ተገለጸ
March 9, 2021
የመንግስት የልማት ድርጅት የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት ስድስት ወራት በአዲስ የቦርድና የማኔጅመንት አባለት እየተመራ 7.3 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ አስታውቋል፡፡ ባንኩ በሀገር ወስጥ ከሚያከናወነው እንቅስቃሴ በተጨማሪ በደቡብ ሱዳንና በጅቡቲ በከፈታቸው ቅርንጫፎ ከፍተኛ ሀብት ማሰባሰብ ማቻሉ የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ በተካሄደበት ወቅት ተገለፀ፡፡
ግምገማውን የመሩት የገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ በሰጡት አስተያየት ባንኩ ራሱን በሰው ሀይልና በቴክኖሎጂ አሳድጎ በሀገር ልማትና እድገት ላይ የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በተጨማሪም የባንኩ የሀብት እድገት ከካፒታል እድገት አንፃር ሲታይ ውጤታማ ቢመስልም በአለምአቀፍ ደረጃ ተዋዳዳሪ ለመሆን በርካታ የማሻሻያ ስራዎች ማከናወን እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዘመናዊ አሰራሮችን በመከተል በተለይም የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት በማስፋፋት ገንዘብ አልባ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየሰራ መሆኑ በግምገማው ወቅት ተብራርቷል፡፡