የኤፍርት ኩባንያዎችን የሚያሰተዳደር ባለአደራ ቦርድ ተቋቋመ

March 8, 2021

ዛሬ የገንዘብ ሚኒሰቴር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ እና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የኤፍርት ኩባንያዎችን የሚያሰተዳደር ሰባት አባላት ያሉት ባለአደራ ቦርድ እንደተቋቋመ ገለፁ፡፡

የኤፍርት ኩባንያዎች ወደ ተለመደው የንግድ፣የአገልግሎት እና የምርት እንቅስቃሴዎች እንዲመለሱ ብሎም በኢኮኖሚ ውስጥ ጉልህ ድርሻ እንዲኖራቸው ለማሰቻል ሰባት አባላት ያሉት ቦርድ በከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲዋቀር ተወስኖል፡፡የባለአደራ ቦርድ አባላቱም የተመረጡት በሙያቸው ያላቸው ብቃት፣በህዝብ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት ብሎም ከፖለቲካ ፓርቲ ገለልተኛ መሆናቸው እንደ መሰፈርት በመወሰድ ነው፡፡

በኤፍርት ድርጅቶች ብሎም በአመራሮች ላይ የፍርድ ማዘዣ እና ምርምራ እየተካሄደ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ከምርመራው ጎን ለጎን በኩባንያዎቹ የሚሰጡ የምርት እና አገልግሎቶች እንዳይቆረጡ ብሎም አስተዳደራዊ ስራዎች እንዲከናውኑ ቦርድ መቋቋም አሰፈላጊ ሆኖ መገኘቱ በመገለጫው ላይ ተጠቀሷል፡፡

ኩባንያዎቹ የተቋቋሙበትን ዓላማ በተለይም ለትግራይ ክልል መልሶ ማቋቋም እና ልማት ለማምጣት ከመሆኑ አንፃር ይህንኑን ለማሳካት በመንቀሳቀስ የክልሉን ማህበረሰብ ከድህነት ለማላቀቅ አስተዋጽኦ እንዲያበክቱ ቦርዱ በከፍተኛ ኃላፊነት እንደሚቀሳቀስ ተገልፆል

510 Views