የከተማና መሠረት ልማት፣ የሰላም እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች የ2016 የበጀት ስሚ ፕሮግራም ተካሄደ

April 25, 2023

ሚያዚያ 17 / 2015 ዓ.ም - የከተማና መሠረት ልማት፣ የሰላም እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮችና ተጠሪ ተቋማት የ2016 የበጀት ስሚ ፕሮግራም በገንዘብ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

የበጀት ስሚ ፕሮግራሙን የመሩት የገንዘብ ሚኒስትሩ ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት የ2016 የበጀት ዕቅድ ዝግጅት ከ2016 እሰከ 2018 ዓ.ም የሚተገበረውን የፕሮግራም በጀት ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አመልክተው ሶስቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እቅዳቸውን አንዲያሳኩ በተቀመጠው የበጀት ጣሪያ መሰረት ገንዘብ ሚኒስቴር በጀቱን አንደሚደግፍ አረጋግጠዋል፡፡



የ2016 በጀት ዘላቂና ፍትሐዊነት ያለው ኢኮኖሚን መገንባትን፣ የዕዳ ክፍያንና የበጀት ጉደለትን እነዲሁም ሌሎች የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳዮችን ባገናዘበ መልኩ የሚዘጋጅ መሆኑን ጠቅሰው ሁሉም የፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች በተሰጣቸው የበጀት ጣሪያ መሰረት በጀታቸውን አዘጋጅተው ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

በበጀት ዝግጅትና አፈጻጸም ሂደት የገሪቱን ሀብትና የመንግስትን በጀት በእቅድ ለተያዘለት አላማ ብቻ በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም እንደሚያስፈልግና አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችና የስራ ሀላፊዎችም በጀትን በአግባቡ የማስተዳደርን ተግባር በከፍተኛ የሀላፊነት ስሜት እንዲወጡም አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

782 Views