የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚውል የ50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
Sept. 20, 2022
መስከረም 10 / 2015 ዓ.ም - ዛሬ በተካሄደ የርክክብ ሰነ-ሰርዓት ላይ የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚውል የ50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለገንዘብ ሚኒስቴር አሰረክቧል፡፡
በርክክብ ስነ-ሰርዓቱ ላይ የተገኙት የገንዘብ ሚኒሰቴር ሚንስትር አቶ አህመድ ሽዴ እንደተናገሩት በቅርቡ የተፈፀመበን ወረራ ለመመከት እየተደረገ ባለው ጥረት ላይ ሁሉም ክልሎች፣የተለያዩ የቢዝነስ ተቋማት እና ህዝቡ ለሀገር ለመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረጉ ይገኛል ብለዋል፡፡
በዚህም መንግስት የተለያዩ ኮሜቴዎች በማዋቀር በአጭር ጊዜ ውስጥ ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ ለማሰባሰብ ያቀደ ሲሆን በእቅዱ መሰረት ተግባረዊ እየተደረገ ነው ሲሉ አቶ አህመድ ሽዴ ገለፀዋል፡፡
የዚህ ድጋፍ አካል የሆነው የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የ50 ሚሊዮን ብር ላደረገው ድጋፍ በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር እና በፌዴራል መንግስት ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ የአቶ ተፈሪ አባተ እንደተናገሩ የደቡብ ክልል መንግስት እና ህዝብ ከዚህ ቀደም ለሁለት ጊዜ በአሸባሪው የህወኃት ቡድን ባደረሰብን ጥቃት እና ወረራ የክልሉ ህዝብ በዓይነትና በገንዘብ ከአንድ ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድረጓል፡፡
የደቡብ ክልል ከዚህ በፊትም በህወሓት የሽብር ቡድን የተከፈተውን የ3ኛ ዙር ጦርነት ለመመከት ሆለታ የእንስሳት ምርምር ማዕከል በመገኘት ከ4520 በላይ የቁም እንስሳት እና የተለያዩ ምግቦችን በገንዘብ ሲተመን 220 ሚሊዮን ብር በላይ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት መለገስ ተችሏል ሲሉ አቶ ተፈሪ አባተ ተናግረዋል፡፡