የገንዘብ ሚኒሰቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞችና አመራሮች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚውል ከ190 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

Aug. 23, 2021

የገንዘብ ሚኒሰቴር እና የተጠሪ ተቋማት ሠራተኞችና አመራሮች የደመወዛቸውን ከ50 እስከ 100 ፐርሰንት ለመከላከያ ሠራዊት ለመስጠት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።

በድጋፍ ማሰብሳቢያ ወቅት የገንዘብ ሚኒሰቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች እንደተናገሩት እናቶቻችንና አባቶቻችን ሉዓላዊነቷንና ክብሯን አስጠብቀው ያስረከቡን ሀገራችን በውስጥና በውጭ ወራሪ ኃይሎች እንዳትደፈር ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድ ሁኖ በጋራ መቆም ይገባል ብለዋል፡፡

አመራር እና ሠራተኞች በየግንባሩ እየተፋለሙ ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣የክልል ልዩ ሀይሎችና ሚሊሻ አባላት በደም ልገሳ፣ በገንዘብና በሞራል ድጋፍ በማድረግ የበኩላችንን ድራሻ እየተወጣን እንገኛለን ሲሉ ገለጸዋል፡፡

በተጨማሪም ይህንን የህልውና ዘመቻ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበትን ሀላፊነት በአግባቡ በመወጣት ለሀገሩ ያለውን ፍቅር በተግባር ሊያሳይ ይገባል ብለዋል፡፡

1113 Views