የገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

By Yonas M. | Published: July 17, 2025

ሐምሌ 10/2017 - የገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ጊዮርጊስ ጫካ በተባለ ቦታ በዛሬው ዕለት አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

የችግኝ ተከላ ፕሮግራሙን ያስጀመሩት የገንዘብ ሚንስትሩ ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት ባላፋት ሰባት ዓመታት መላው የመንግስት ሰራተኛ፣ አመራር፣ የንግዱ ማህበረሰብና ህዝብ በጋራ በተደራጀ መልኩ በአረንጓዴ አሻራ መሳተፋ አረንጓዴ የደን ሽፋንን ማሳደጉንና ከተሞችን ፅዱ ማደረጉን፤ እንዲሁም በዚህ መርሀ ግብር ለምግብነትና ለወጪ ንግድ ጠቃሚ የሆኑ ችግኞች ተተክለው አሁን ላይ ውጤት ማምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

ክቡር ሚንስትሩ እንዳሉት እስካሁን በአረንጓዴ አሻራ የህዝብ ጉልበትንና ዕውቀትን በመጠቀም የተሰራው ስራ በገንዘብ ቢሰላ በብዙ መቶ ቢለየን ብር የሚገመት ስራ መከናወኑን ተናግረው፤ በመደበኛው የበጀት አሰራር ይሰራ ቢባል ከአቅም በላይ ይሆን አንደነበር አመልክተዋል፡፡

ክቡር ሚንስትሩ ሁሉም ሰው የሚችለውን ያህል ችግኝ በአግባቡ በመትከልና በመንከባከብ ሀላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

55 Views