የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች 3ሺ ችግኞችን ተከሉ

July 17, 2023

 

ሀምሌ 10 / 2015 ዓ.ም - የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች የገንዘብ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ትብብር ዘርፍ ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው በተገኙበት በእንጦጦ ተራራና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ 3ሺ ችግኞችን በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

‹‹ነገን ዛሬ እንትከል›› በሚል መሪ ቃል በአንድ ቀን 500 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል በተያዘው መርሀግብር መሰረት ዛሬ ሀምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ቁጥራቸው ከ500 በላይ የሆኑ የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ሰራተኞችና አመራሮች በእንጦጦ ተራራ ላይና በገንዘብ ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ ውስጥ ችግኞችን ተክለዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ ጉዳይ ኢትዮጵያን የመጠበቅ፣ የማክበር፣ የማበልጸግ፣ ታሪክ የመቀየርና ለትውልድ የመትረፍ ጉዳይ በመሆኑ የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ሰራተኞችና አመራሮች በዚሁ መንፈስ ችግኞችን በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል 

 

617 Views