የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
Published: Feb. 19, 2026
የካቲት 11 / 2018 ዓ.ም - የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት የ2018 በጀት አመት የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ የየተቋሟቱ ከፍተኛ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄዷል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ የግምገማ መድረኩን ሲከፍቱ እንደገለጹት የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ ዘንድሮ ሁለተኛ አመቱን መያዙን ጠቅሰው በአፈፃፀሙ ከፍተኛ እድገት መረጋጋጡን፣ የዋጋ ንረት ከነበረበት ሁለት አሐዝ ወደ ነጠላ አሀዝ ማለትም ወደ 9.7 በመቶ መውረዱን ገልጸው በዚህም የገበያ ዋጋን ማረጋጋት መቻሉን፣ ምርትና ምርታማነት እድገት ማሳየቱን የፍላጎትና የአቅርቦት ልዩነት እየጠበበ መምጣቱን አስረድተዋል፡፡
የዋጋ ንረቱ ወደ ነጠላ አሀዝ ሊወርድ የቻለው መንግስት ጥብቅ የፊስካልና የገንዘብ ፖሊሲ ተግባራዊ በማድረጉ መሆኑን ጠቁመው በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት የመንግስት ገቢ ማደጉንና የመንግስት የበጀት ጉድለት ከበብሄራዊ ባንክ ምንም አይነት ቀጥተኛ ብድር ሳይወሰድ ከመንግስት ግምጃ ቤትና ከልማት አጋሮች በተገኘ ገንዘብ መሸፈኑን አስረድተዋል፡፡
በመደረኩም የመጀመሪያው 6 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በየመ/ቤቶቹ ከቀረበ በኃላ በቀረቡት ጥያቄዎችና አሰተያየቶች ላይ ከመድረኩ ተገቢው ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የስድስት ወር አፈጻጸም ተገምግሟል፡፡
በመጨረሻም በሚቀጥሉት የበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት የተመደበው ሀብት በአግባቡ ለታለመለት አላማ እንዲውል ለማስቻል፣ የቀጣይ ዓመት የበጀት ዝግጅትን በአግባቡ መምራት እና ከበጀት ድጋፍ ጋር የተገነኙ የሪፎርም ሥራዎችን መምራትና አፈፃፀሙን መከታተል እንደ ቀጣይ አቅጣጫ በመስቀመጥ መደረኩ ተጠነቋል፡፡