የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ከፈረንሳይ የንግድ ሚኒስቴር ጋር ተወያዩ

Feb. 7, 2023

 

ጥር 30 / 2015 ዓ.ም - የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በፈረንሳይ በሚያደርጉት የስራ ጉብኝት ከፈረንሳይ የንግድ ሚኒስተር ከሚስተር ቤች ኦሊቪዬር ጋር በሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚ ትብብርና በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ፍሪያማ ውይይት አደረጉ፡፡

በውይይታቸው ወቅት ክቡር ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ለሚስተር ኦሊቪዬርና ለፈረንሳይ ከፍተኛ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት እያከናወነችው ስላለው አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ በግጭት አካባቢዎች እየተከናወነ ስላለው የመልሶ ማቋቋም ጥረትና ስለሰላም ስምምነቱ አተገባበር ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተው ዘላቂ የልማት አጋር የሆነችው ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ ስለምትሰጠው የልማት ድጋፍና ትብብር አመስግነዋል፡፡

የፈረንሳይ የንግድ ሚኒስትር ሚስተር ቤች ኦሊቪዬር በበኩላቸው የፈረንሳይና የኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ትብብር ከምእተ አመት በላይ ያስቆጠረ ታሪክ ያለው መሆኑን ጠቅሰው በቅርቡ የተፈረመው የሰላም ስምምነት ውጤታማ እንዲሆን፣ የመልሶ ማቋቋሙ ጥረት እንዲሳካና የኢኮኖሚ ማሻሻያው የታለመለትን ግብ እንዲመታ ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በወይይቱ ወቅት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ ክቡር አቶ ማሞ ምህረቱ መገኘታቸውም ታውቋል፡፡

1221 Views