ያለ አገልግሎት ተከማችተው የሚገኙ የመንግስት ንብረቶች ምዝገባና አወጋገድ ንቅናቄ ከሚያዚያ 4 እሰከ 8 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገለፀ

March 22, 2021

ከሚያዚያ 4 እሰከ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ የመንግስት ንብረቶች ምዝገባና አወጋገድ ንቅናቄ ይካሄዳል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚካሄደው ያለ አገልግሎት ተከማችተው የሚገኙ የመንግስት ንብረቶች ምዝገባና አወጋገድ ንቅናቂ ዙሪያ ላይ ከፌዴራል ባለበጀት መሰሪያ ቤቶች እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ዛሬ በገንዘብ ሚኒስቴር ውይይት ተካሄደ፡፡

በውይይቱም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዙሪያ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በመለየት፣ የመፍትሔ ሃሳቦችን ማመንጨት እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን በጋራ ማስቀመጥ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡

የገንዘብ ሚኒሰቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ የመንግስት ሀብት ለታለመለት ዓለማ እንዲውል እንዲውልና ሲወገድም በዕቅድና ለመንግስት ጥቅም ሊያስገኝ በሚያስችል መልኩ ተቋማት በሚሰጣቸው መመሪያ መሰረት ሊተገብሩት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በቀጣይነትም ንብረቶቹ ከተመዘገቡ በኋላ ለተጠቃሚ አካላት በማስተላለፍ እና በሽያጭ በማስወገድ ላይ መንግስት በአትኩሮት እንደሚሰራ በውይይቱ ተብራርቷል፡፡

1027 Views