ገንዘብ ሚኒሰቴር የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያሰመዘገበ ላለው አመርቂ የስራ አፈጻጸም ምሰጋና አቀረበ

March 9, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013 ገንዘብ ሚኒሰቴር በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ላይ ያሳደረውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን በመጠቀም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስለወሰዳቸው እርምጃዎች ምስጋና አቀረበ፡፡

ዛሬ የአየር መንገድ የስራ አፈጻጸም በገንዘብ ሚኒሰቴር በተገመገመገበት ወቅት ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ የአየር መንገዱ አመራር በወሰዳቸው ፈጣንና ፈጠራ የተሞላበት እርምጃዎች አሁን ለተገኘው ውጤት ወሳኝ ሚና እንደነበራቸው ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ሚኒስትሩ በአየር መንገዱ የተደሰዱ የአመራር ውሳኔዎች አየር መንገዱን ከአፍሪካ አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ እንዲሆን እንዳስቻለው ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም ሪፖርታቸውን ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት አየር መንገዱ ቢዘህ ወቅት ውጤታማ መሆን የቻለው የቦርዱ አመራር፣ አስተዳደር አካለትና ሰራተኞች ቁርጠኛና ጠንካራ የስራ ባህል ስላላቸው እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በዚህ ወቅት ሌሎች አየር መንገዶች ኪሳራ ሲደርስባቸውና ሰራተኞቻቸውን ሲበትኑ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በማስፋፋትና ትኩረቱን በመለዋወጥ በተለይም የካርጎ፣ የጥገና እና የሆቴል አገልግሎቶችን በስፋት በማከናወን የተሻለ ገቢ ማግኘት ችሏል፡፡ አቶ ተወልደ በተጨማሪም እንደገለፁት ኤርፖርቶች እና ተርሚናሎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በቀጣይነት እንደሚገነቡ ገልፀዋል፡፡

አየር መንገዱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን በመከላከል የመንገደኞቹንና የሰራተኞቹን ጤንነት ለመጠበቅ የተለያዩ እርምጃዎችን በመወሰድ የሰው ህይወት በማዳን ለሎሎች ተቋማት ተምሳሌት እንደሆነ በግምገማው ወቅት ተብራርቷል፡፡

729 Views