ገንዘብ ሚኒስቴር መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች ያለምንም የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ በቀጥታ እንዲገቡ ወሰነ
April 9, 2022የገንዘብ ሚኒስቴር መሰረታዊ የምግብ ሽቀጦች የሆኑት ዘይት፣ስንዴ፣ስኳር፣የህጻናት ወተት እና ሩዝ ያለምንም የውጭ ምንዛሬ ፍቃድ (በፍራንኮ ቫሉታ) በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል በቀጥታ እንዲገቡ ወሰነ፡፡
መንግስት በአሁኑ ወቅት እየተስተዋለ ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት እንዲቻል እና በርካታ የውጭ ሀገር የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ኢትዮጵያዊያን የራሳቸውን ሚና መጫወት እንዲችሉ የፍራንኮ ቫሉታ ፈቃድ በተፋጠነ ሁኔታ እንዲፈቀድላቸው ጥያቄ እያቀረቡ በመሆኑ ነው፡፡
ቀርጥና ታክሱ በሚመለከት በገንዘብ ሚኒስቴር በ22/3/2013 ዓ.ም በቁጥር ማአ.30/7/51 በተጻፈው ደብዳቤ መሰረት እንዲፈጸም ፤ አፈጻጸሙን በተመለከተ ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት በኩል ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግበት ተወስኗል፡፡