20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በገንዘብ ሚኒስቴር ተከበረ

Published: Dec. 1, 2025

ሕዳር 22 / 2018 ዓ.ም - የገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን ዴሞክራዲያዊ መግባባት ለህብረብሄራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል በሚኒስቴሩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አከበሩ፡፡

በበአል አከባበሩ ላይ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስተር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ እንደገለጹት ኢትዮጵያ የብዝሀነት ሀገር መሆኗን አመልክተው በየአመቱ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን መከበሩ በሀገሪቱ ህዝቦች መካካል ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነትና እህትመማችነትን ማጎልበቱን አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የብዝሀነት አገር እንደመሆኗ ሲቪል ሰርቪሱም ኢትዮጵያን በሚመስል መልኩ ብዝሀነትንና አካታችነትን ያረጋገጠ ሊሆን እንደሚገባና ዴሞክራሲን ባህል በማድረግ ፌደራላዊ ህብረ ብሄራዊነታችንና አንድነታችንን ማጠናከር ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

በበአል አከባባሩ ላይ ዴሞክራሲና ፌዴራላዊ ሥርአት በኢትዮጵያ - ተስፋዎቹና ተግዳሮቶቹ እንዲሁም ብዝሀነትንና አካታችነትን ያረጋጋጠ የሲቪል ሰርቪስ ግንባታ በሚሉ ርእሶች ጥናቶች ቀርበው በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

12 Views