የካቲት 22 2014ዓ.ም - ኢትዮጵያና ጣሊያን ለዜጎች መረጃ ምዝገባ አገልግሎት የሚውል የአንድ ሚሊዮን ዩሮ ( 56,967,900 ብር ) የእርዳታ ስምምነት በሂልተን ሆቴል ተፈራረሙ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም በገንዘብ ሚኒስቴርና በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዛሬ የካቲት 22 2014 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል በተገመገመበት ወቅት የድርጅቱ ምክትል ዋና ስራ አሰፈፃሚ አቶ ኢሳያስ ወልደ ማሪያም እንዳስታወቁት ድርጅቱ ከመሰል ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ድርጅቶች አንጻር በተለያዩ መመዘኛዎች ሲታይ የላቅ ዕድገት አሳይቷል፤ ትርፋነቱም በዚህ አስቸጋሪ ወቅትም ቀጥሏል ብለዋል፡፡
የኢትዮ- ቴሌኮም የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ዛሬ የካቲት 21 2014 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል በገንዘብ ሚኒስቴርና በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር በተገመገመበት ወቅት የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የድርጅታቸው አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥር 60 ነጥብ 8 ሚሊየን መድረሱን አስታውቀዋል፡፡
በገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ በክብርት ወ/ሮ ሰመሬታ ሰዋሰው የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ እና በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት ስር የሚገኙት የቡልቡላ እና የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጎብኝቷል፡፡
Copyright © 2021 MOF All Right Reserved