የኢትዮጵያና የኩዌት ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት በሁለቱ ሀገራት የገንዘብ ሚንስትሮች መካከል ተደረገ
Dec. 2, 2021
የኢፌዲሪ የገንዘብ ሚንስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴና የኩዌት አቻቸው ክቡር ከሊፋ ሙሳዱ ሀማዳ ሁለቱ ሀገራት በቀጣይ በንግድና መዋዕለ ነዋይ ፍሰት ላይ በጋራ መሰራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል፡፡
ኢትዮጵያና ኩዌት ካላቸው ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ባለፈ ብዛት ያላችው በኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ልማት ላይ ጠንካራ ተሳትፎ እያደረጉ እንዳሉ ይታወቃል፡፡