የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች በሲዳማ ክልል የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

July 29, 2021

በክቡር አቶ አህመድ ሺዴ የገንዘብ ሚኒስትር የሚመራው የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋማት እንዲሁም የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሰራተኞችና አመራሮች ልኡካን ቡድን በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአርቤጎና ወረዳ በአረንጓዴ አሻራ ማኖር መርሀ ግብረ የችግኝ ተከላና የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ተግባር አከናውኗል፡፡

የልኡካን ቡድኑ ከሐምሌ 16 አስከ ሐምሌ 19 2013 ዓ.ም በወረዳው ባከናወነው የአረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሀ ግብር 10ሺ አገር በቀል የዛፍ ችግኞችን የተከለ ሲሆን ከአረንጓዴ አሻራ የማኖር ፕሮግራም ጎን ለጎን ደግሞ በአንድ ሚሊዮን ብር ወጪ የአስር አቅመ ደካማ ዜጎች ቤቶችን ግንባታና እድሳት አከናውኗ፡፡

የሲዳማ ብሄራዊ ክልል መንግስት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ ለልኡካን ቡድኑ ደማቅ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎችም በሲዳሚኛ ‹‹ ዳኤ ቡሹ ›› እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ለክቡር አቶ አህመድ ሺዴ፣ ለተጠሪ ተቋማትና ለልማት ድርጅቶች አመራሮች የሲዳማን ባህላዊ አልባሳት በገጸበረከትነት አበርክተውላቸዋል፡፡

270 Views