“ሱፐር ክላስተር ሰርቨርስ” የተባለውን የኤሌክትሮ መካኒካል ስራዎች አቅርቦት ለማግኘት ከኢኮዲሱሥኮ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

Aug. 5, 2021

 

ሐምሌ 28 /2013 ዓ.ም፡- በዕለቱ በተካሄደው የፊርማ ስነ ስርዓት ላይ እንደተገለጸው፣ ሚኒስቴሩ የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ስርዓት /አይ ኤፍ ኤም አይ ኤስ/ አቅሙን ለማጎልበት የሚያስችለውን የ “ሱፐር ክላስተር ሰርቨርስ” ወደ ስራ ለማስገባት የኤሌክትሮ መካኒካል ስራዎች አቅርቦት በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አማካኝነት የሚያገኝ ይሆናል፡፡

ሚኒስቴሩን በመወከል የኮርፖሬት ዳይሬክተር ጀኔራል የሆኑት አቶ ግዛው ኃይሉ ፤ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በኩል ደግሞ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኢንጂኒየር ነገደ አባተ ስምምነቱን ዛሬ በመ/ቤቱ አዳራሽ ተፈራርማወል፡፡

ለተጠቀሰው የኤሌክትሮ መካኒካል አቅርቦት ማስፈጸሚያ የብር 26 ሚሊዮን ስምምነት የተደረገ ሲሆን ስራውንም በሶስት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ መታቀዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ስርዓት /አይ ኤፍ ኤም አይ ኤስ/ የመንግስት የፋይናንስ አስተዳደርን ውጤታማነት በማሻሸሻል የመንግስት ተቋማት ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንዲችሉ ለማገዝ ታስቦ በመተግበር ላይ የሚገኝ የመረጃ ስርዓት ነው፡፡ በዚህ የተቀናጀ የመረጃ ስርዓት ባልታቀፉ ቀሪ 60 የፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች በተያዘው የ2014 በጀት ዓመት የመረጃ ስርዓቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻልም በሚኒስቴሩ ዕቅድ ተይዟል፡፡

1073 Views