የ122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ተዘጋጀ

Dec. 30, 2021

በገንዘብ ሚኒስቴር የተዘጋጀው የ122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡

ተጨማሪ በጀቱ ለሀገር ደህንነት ማስጠበቂያ፣ ለሰብአዊ እርዳታ፣ በጦርነትና ግጭቶች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ማቋቋሚያ እንዲሁም ለሌሎች አስፈላጊ የመንግስት ስራዎች ማስፈጸሚያ የሚውል ነው፡፡

ተጨማሪ በጀቱን ማዘጋጀት ያስፈለገው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ተጨማሪ ወጪ በማስፈለጉ፣ መንግስት በሚሰበስበው ገቢ አሁን ያለውን የክፍያ ጥያቄ መመለስ አስቸጋሪ በመሆኑ እንዲሁም የተጨማሪ ወጪ ፍላጎትን በበጀት ሽግሽግ ማስተናገድ አዳጋች በመሆኑ ነው፡፡

የተጨማሪ በጀት ጥያቄው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት እንደ ጸደቀ በቀጥታ ስራ ላይ እንደሚውል ታውቋል፡፡

1059 Views