በኢትዮጵያና በሲዊዘርላንድ መንግስታት መካከል ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት ስምምነት ተፈረመ
July 29, 2021በኢትዮጵያና በሲዊዘርላንድ መንግስታት መካከል ተደራራቢ ግብርን ለማስወግድ የሚያስችል ስምምነት ዛሬ ሐምሌ 22 2013 ዓ.ም በገንዘብ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተፈረመ፡፡
የስምምነቱ አላማ የሲዊዘርላንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ሀብታቸውን በልማት ስራ ላይ እንዲያውሉ ለማበረታታትና የኢትዮጵያም ባለሀብቶች በሲዊዘርላድ ገበያ ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማስቻል መሆኑን ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ የገንዘብ ሚኒስትር አስታውቀዋል፡፡
ተደራራቢ ግብር ለውጭ ኢንቨስትመንት ማነቆ በመሆኑ ከሲዊዘርላንድ መንግስት ጋር ሶስት ዙር ድርድር በማድረግ የተደራራቢ ግብርን ለማስገድ መግባት ላይ ተደርሷል፡፡
የተደራራቢ ግብር ማስወገድ ስምምነት የውጭ ኢንቨስትመንትን ለማበረታት የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ የግብር ማጭበርበርን በመከላከል ገቢ ለሀገር ልማትና እንድገት እንዲውል የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለውም ይታወቃል፡፡
የተደራራቢ ግበር ማስወገድ ስምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የፈረሙት የገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሲሆኑ በሲዊዘርላንድ በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ የሲዊዘርላንድ አምባሳደር የተከበሩ ታማራ ሞና ናቸው፡፡
የፊርማው ስነስርዓት ሲጠናቀቅም የሁለቱ ሀገራት ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡