በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ የኢትዮጵያን የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደርን ለማሻሻል የሚያግዝ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

Aug. 3, 2023

ሐምሌ 27/ 2015 - በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ የኢትዮጵያን የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደርን ለማሻሻልና ለማዘመን የሚያግዝ ፕሮጀክት በገንዘብ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደ የውይይት መድረክ ይፋ ተደረገ፡፡

በሚቀጥሉት አራት አመታት ውስጥ ተግባራዊ በሚደረገው ፕሮጀክት የተጠቃሚ ተቋማትን የአመራር አቅም የማጎልበት፣ የተሻሻለ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር አገልግሎትን በታችኛው የመንግሰት እርከን የማስፈን፣ በተቋማት የበጀት አስተዳደርንና ክትትልን የማሻሻልና የመንግሰት ግዢ አገልግሎት ተቋማዊ አቅምን የማሳደግ ተግባር በፕሮጀክቱ ድጋፍ ሰጪ የቴክኒክ ቡድን እንደሚከናወን ታወቀወል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው እንደገለጹት የቴክኒክ ድጋፍ ቡድኑ የመንግስት የፋይናንስ አስተዳደር መሻሻያን ተግባራዊ በማድረግ ላይ የሚገኙ ተቋማትን አቅም በመገንባትና ቴክኒካዊ ድጋፍ በመስጠት ዓይነተኛ ሚና ይጫወታል የሚል ዕምነት እንዳለቸው ተናግረዋል፡፡

ይህን የቴክኒክ ድጋፍ በቀጣዩ አራት ዓመት ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል የአውሮፓ ህብረት በአጠቃላይ የአስር ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ መመደቡም ታውቋል፡፡

329 Views