የጃፓን መንግስት ለተንቃሳቃሽ የተሽከርካሪ ክሊኒክ ግዢ የሚውል 185 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

Sept. 28, 2022

መስከረም 18/2015 - የጃፓን መንግስት በኢትዮጵያ በመንቀሳቀስ የተሸከርካሪ ላይ የህክምና አገልግሎት ለሚሰጡ መኪኖች ግዢ የሚሆን የ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ወይንም የ185 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡  

እየተንቀሳቀሱ የህክምና አገልግሎት የሚሰጡት የተሸከርካሪ ክሊኒኮች ኤሌክትሮ ካርዲዮግራፍ፣ አልትራ ሳውንድና ሌሎች ዘመናዊ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች የተገጠሙላቸው መሆናቸው ታውቋል፡፡

ይህ ድጋፍ በዋናነት በአፋር፣ በሶማሌ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላና በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልሎች አርብቶ አደር አካባቢዎች ከጤና ተቋማት ርቀው የሚገኙ ሴቶችን ይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ተገልጽዋል፡፡

የእርዳታ ስምምነቱን በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የገንዘብ ሚንስቴር ሚንስትር ዲኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰውና በጃፓን መንግስት በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሚስስ ኢቶ ታካኮ ፈርመውታል፡፡

 

1147 Views