የገንዘብ ሚኒስቴር በመሰረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት የጋር የግምገማ መድረክ አካሄደ

June 1, 2023

ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የገንዘብ ሚኒስቴር በመሰረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦቶች በተከናወኑ ስራዎች ላይ የልማት አጋሮች ፣የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደሮችን ያካተተ የጋራ የግምገማ  መድረክ በሂልተን ሆቴል አካሄደ፡፡

በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ  ወይዘሮ ሰመሪታ ሰዋሰው÷የኢትዮጵያ መንግስት አለም ባንክን ጨምሮ ከተለያዩ የልማት አጋሮች በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የጋራ ተጠቃሚነትንና ፍትሃዊ አገልግሎትን ባልተማከለ ደረጃ  በመስጠት በትምህርት፣በጤና፣በውሃ፣በግብርና እና በገጠር መንገድ መሰረታዊ አገልግሎቶች አሰጣጥን የሚያሳድጉ ሰራዎችን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

የመርሃ ግብሩ ትግበራ ሂደት ፍትሃዊ የሆነ የመሠረታዊ አገልግሎት ተጠቃሚነትን በማሻሻል እና በክልሎች ደረጃ ተጠያቂነትን እንዲሰፍን በማደረግ ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡

ሚኒስትር ዲኤታዋ እናደተናገሩት  በፕሮግራሙ ትግበራ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ  ግጭት፣ ድርቅና የኮርና ወረርሽን ተግዳሮቶች  ቢያግጥሙም ከልማት አጋሮች የሚገኘውን የውጭ ሀብት በግጭት የተጎዱ ዜጎችን መልሶ በማቋቋምና በሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች በማዋል አሳታፊ የሆነ አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አሰረድተዋል፡፡

የመሰረታዊ አገልግሎትን በፍትሀዊነት በሁሉም ክልሎች ለሚገኙ ዜጎች ለማዳረስ መንግስት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ወ/ሮ ሰምሪታ ሰዋሰው ገልፀዋል፡፡

የመሰረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት ባለፉት ዓመታት በፌደራል መንግስት፣ በልማት አጋሮች፣ በክልሎች፣ በወረዳዎች ትምህርትን፣ ጤናን፣ የገጠር መንገድን፣ ግብርናንና የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እንዲሁም የአካባቢንና የግል ንፅህናን ለማስፋፋትና ጥራቱን ጠብቆ እንዲሰጥ ለማስቻል ተግባራዊ ሲደረግ የቆየ የልማት ፕሮግራም ነው፡፡

928 Views