የገንዘብ ሚኒስቴር አመራር እና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ አደረጉ

Aug. 16, 2021

በገንዘብ ሚኒሰቴር የተካሄደው የደም ልገሳ "ደማችን ለመከላከያ ሠራዊታችን" በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተደረገ ያለው ንቅናቄ አካል ነው፡፡

በደም ልገሳው ወቅት ያናገርናቸው የገንዘብ ሚኒሰቴር ሰራተኞች እና አመራሮች ውዱን እና በገንዘብ የማይተመነውን ደም፤ለሀገር መከላከያ ሰራዊት በመለገሳቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ጠቁመው የህግ ማስከበር ዘመቻው እስኪጠናቀቅ ድረስም ድጋፋችን ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአሁኑ ወቅት ከሀገር መከላከያ ስራዊት ጎን በመሆን ሃገርን ለማዳን የተጀመረው የህልውና ዘመቻ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፉን መቀጠል እንዳለበት የገንዘብ ሚኒሰቴር ሠራተኞች አሳሰበዋል፡፡

841 Views