የገንዘብ ሚኒስቴር የወንዶች እግር ኳስ ቡድን የስፖርት ለሁሉም ፌስቲቫል ዋንጫን አሸነፊ ሆነ

April 9, 2024

በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከየካቲት 14 እስከ መጋቢት 27 ድርስ ሲካሄድ የነበረው ስፓርታዊ ውድድር የገንዘብ ሚኒስቴር የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ከማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለፍፃሜ ቀርቦ በመደበኛ የጨዋታ ጊዜ 0ለ0 በመጠናቀቁ ጨዋታው ወደ መለያ ምት አምርቶ ገንዘብ ሚኒስቴር 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡

በውድድሩ ላይ የእግር ኳስ ቡድኑ በሁለተኛ ዲቪዚዮን የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ከተደለደሉት 16 ቡድኖች ጋር በሦስተኛ ምድብ ከአዲስ ሚዲያ ኔቶርክ፣ ከጉሙሩክ ኮሚሽን እና ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር ተደልድሎ ከምድቡ 6 ነጥብ በማግኘት ወደ ቀጣይ ዙር ማለፍ ችሏል፡፡

ቡድኑ በእሩብ ፍፃሜው እና በግማሽ ፍፃሜው ውድድር ላይ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴርን በማሸነፍ ለ17ኛው ስፖርት ለሁሉም ፌስቲቫል የወንዶች የእግር ኳስ የፍፃሜ ጨዋታ ደርሷል፡፡

ለዋንጫ በተደረገው ፍልሚያ ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር የተገናኘው የገንዘብ ሚኒስቴር የእግር ኳስ ቡድን ጨዋታው በመደበኛው ሰዓት 0-0 በማጠናቀቁ  አሸናፊውን ለመለየት በተደረገው የፍፁም ቅጣት ምት ቡድኑ 3-1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የውድድር አመቱ የስፖርት ለሁሉም ፌስቲቫል አሸናፊ በመሆን የወርቅ ሜዳላይ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ዳንኤል ገ/ጊዮርጊስ ከጨዋታ ፍጻሜ በኃላ በሰጡት አሰተያየት ቡድን በተለያዩ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ በርካታ ልምዶችን በመቀሰም እና በመከላከል የተመሰረተ አጨዋወትን መከተሉ ውጤታማ እንዲሆን አስችሏታል ሲሉ ገለፀዋል፡፡ በቀጣይም ተቋሞን የሚመጠን እግር ኳስ ቡድን ለመገንባታ እየተሰራ ይገኛል ብልዋል፡፡

ይህ በእንዲ እንዳለ ገንዘብ ሚኒስቴር በውድድሩ ላይ ከወንዶች እግር ኳስ በተጨማሪም በሴቶች መረብ ኳስ  ዉድድር ላይ ተሳትፎ አድርጓል፡፡

በመክፈቻው ስነ-ሰርዓት በተደረገ እንቁላል በአፍ ይዞ በተደረገ የ100 ሜትር የሩጫ ውድድር መ/ቤታችንን ወክለው የተሳተፉት ታሪኬ ግንባር እና አማኑኤል ግዛቸው የወርቅ መዳሊያ እና የነሃስ መዳሊያ ተሸላሚ በመሆን አጠናቀዋል፡፡

በመጨረሻም የሉዕካን ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ መሪሳ በ2016 ዓ.ም የፌደራል መስሪያ ቤቶች ስፖርታዊ ፌስቲቫል ላይ ቡድኑ ውጤታማ ተሳትፎ እንዲኖረው ላደረጉ ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

 

 

 

 

3285 Views