የገንዘብ ሚኒሰቴር ያዘጋጀውን የህጻናት ማቆያ አስመረቀ
Jan. 28, 2022
የገንዘብ ሚኒሰቴር ለሰራተኞቹ ልጆች ያዘጋጀውን ሕፃናት ማቆያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በይፋ አስመርቋል፡፡ የህፃናት ማቆያው ከ4 ወር- 3 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ልጆች አገልግሎት ይሰጣል፡፡
በምረቃው ላይ የተገኙት ክብርት የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው እንደተናገሩት በስራ አከባቢ የህጻናት ማቆያዎች እንዲዘጋጅ መደረጉ ሴቶች በስራቸው ስኬታማ እንዲሆኑና የተዋዳዳሪነት መንፈስ እንዲያዳብሩ ያስችላቸዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው ዕለት የተመረቀው የህፃናት ማቆያው በሚኒሰቴር መስሪያ ቤቱ ለሚገኙ ሴት ሰራተኞች ልጆቻቸውን በቅርበት ሆነው አስፈላጊውን ክትትል ለማድረግ ዕድል የሚፈጥርላቸው እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡